Saturday, 12 May 2018

የልጅዎን የምግብ ፍላጎት ለመጨመር የሚረዱ 12 ጠቃሚ ምክሮች



የልጆች የምግብ ፍላጎት ማጣት ለበርካታ ወላጆች አስቸጋሪና አሳሳቢ ችግር እየሆነ መጥቷል። አንዳንዴም ቤተሰቡ ውስጥ ውጥረትን ሲፈጥር ይስተዋላል። ወላጆችም ልጆችን እያታለሉ ከመመገብ እስከ ቁጣና ማስፈራራት ድረስ የሚደርሱ መንገዶችን በመከተል ልጀቻቸውን ለመመገብ ሲጥሩ ይታያል። ይህንን ችግር ለመቅረፍ የሚረዱና የምግብ ፍላጎትን ለመጨመር የሚረዱ ሳይንሳዊ መንገዶች እነሆ  ብለናል ። ያንብቡና ለሌሎችም ያጋሩ።

1.  ልጅዎ ሁል ጊዜ ቁርስ  መመገቡን ያረጋግጡ
ጥሩ እና ጤናማ ቁርስ መመገብ የልጅዎን    የመመገብ ፍላጎት ይጨምራል።

2.  ልጆች ምግብ ከመውሰዳቸው  ከ30 ደቂቃዎች በፊት ውሃ ይስጧቸው
ልጆች ማለዳ ከመኝታቸው እደተነሱ ወተት ከመጠጣታቸው በፊት  ውሃ እንዲጠጡ ይመከራል ። በተጨማሪም ምግብ ከመጀመራቸው  ከግማሽ ሰዓት በፊት ውሃ ቢሰጣቸው የምግብ ፍላጎታቸ እንዲጨምር ያደርጋል።

 3. ወተት ብዛት አይመገቡ
ጥቂት የምግብ ፍላጎት ያላቸው ብዙ ሕፃናት 'በጣም ብዙ ወተት' የመጠጣት ልምድ አላቸው ። ይህም የምግብ ፍላጎታቸውን የባሰ ሊቀንሰው ይችላል ። በመሆኑም የወተት መጠን በመቀነስ በሌሎች ተመሳሳይ ፈሳሽ ምግቦች ይተኩላቸው ።

4. የሚወዱትን ምግብ ይስጧቸው
የምግብ ፍላጎት ችግር ያለባቸው ልጆች አንዳንድ ጊዜ የሰለቻቸውን የምግብ አይነት መመልከት ሁሉ ሲያስጠላቸው ይታያል ።
ይህ የልጅዎ ሁኔታ ከሆነ የምግብ።ፍላጎታቸውን ለማነሳሳት በመጀመሪያ የሚወዱትን የምግብ አይነት መጀመሪያ ላይ ለማቅረብ ይሞክሩ።


5. በትንሽ በትንሹ  ይስጧቸው
ለመጀመሪያ ጊዜ በጣም ትንሽ የምግብ መጠን ይስጧቸው ። ይህ ትንሽ የምግብ ይዘት በተራው የምግብ ፍላጎት ያሻሽላል ።
ለልጆች ጥቂት ምግብ ብቻ ይስጡ ይህም ቀስ በቀስ የምግብ ፍላጎታቸው ይጨምራል.
እራሳቸውን በራሳቸው መብላት እስኪጀምሩ እና በእራሳቸውን  መጠን እስኪወስዱ ድረስ ትንሽ ትንሹን መስጠት አለብዎ።

6. ቅባት የበዛበት ምግቦ አይስጧቸው
ምክንያቱም የበዛ የቅባት ይዘት የልጅዎን  የምግብ ፍላጎት የባሰ እንዲቀንስ ያደርጋል ።

7.  ልጅዎን እንዲጫወትና እንዲንቀሳቀስ ያድርጉ
ስፖርት መስራትና ብዙ ሀይል እንደሚወስድ የታወቀ ነው  ይህም የምግብ ፍጆችን  እንዲጨምር ያደርጋል።
ልጅዎ ዝቅተኛ የምግብ ፍላጎት ካለው የጨዋታ ጊዜውን ይጨምሩ ረሃብ ተመልሶ ሲመጣ ያዩታል!

8. በጣም ሞቃት ከሆኑ  አየር እንዲገባ ያድርጉ
አዎ እውነት ነው! በቤት ውስጥ በጣም ሞቃት  ከሆነ የምግብ ፍላጎት ይቀንሳል። ልጅዎን በሚመግቡበት ወቅት ክፍት መስኮት አጠገብ በመሆን ንጹህ አየር እንዲገባ ያድርጉ ለውጡን ያስተውሉታል።

9. ትኩስ የሎሚ ጭማቂ ይስጡ
 የሎሚ ጭማቂ የመመገብን እና የምግብ ፍላጎትን ያሻሽላል።

10. በምግብ ሰዓት ጭንቀቶች ያስወግዱ
በምግብ ጊዜያትአላስፈላጊ ጭንቀቶችን ያስወግዱ ። ልጄ ምግብ አልበላ አለ በማለት የሚያሳዮት ጭንቀት የልጆችን ስሜት ሊረብሽና የባሰ ፍላጎታቸውን ሊቀንስ ይችላል ።

11. የዚንክ ንጥረ ነገርን ይጨምሩ
ዚንክ የምግብ ፍላጎት ለመገንባት ይረዳል። የስንዴና የለውዝ  ዘሮች በሰውነት ውስጥ የዚንክ ደረጃ ለማሻሻል ጥሩ ናቸው። በልጅዎ ምግቦች  ውስጥ እነዚህን ነገሮች ማካተት ይሞክሩ።

12. አትክልትና ፍራፍሬን አዘውትረው ይመግቡ
አትክልትና ፍራፍሬ  ምግቦች የምግብ ፍላጎት ለመገንባት ይረዳሉ።  ምግብን በማዋሃድ ሜታቦሊዝም እንዲጨምር ይሠራሉ ።

በመጨረሻም ልጅዎ እጅግ የከፋ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ችግር ካለበት ሀኪምዎን ማማከር አይርሱ ።

No comments:

Post a Comment

"ምግብ የሚያስቸግሩ ልጆችን እንዴት እንመግባቸው" - ዶ/ር ንጉሤ ጫኔ ፤ የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም

ከአንድ እስከ ሦሥት ዓመት ያሉ ልጆች መደበኛ አመጋገብ የላቸውም። አንድ ቀን በድንብ ይበላሉ ሌላ ቀን ደግሞ ፈጽመው ምግብ መንካት አይፈልጉም። ቁርስ በደንብ በልተው ምሳ ላይፈልጉ ይችላሉ። ይህ የተለመደ ፀባያቸው ስለሆነ ...