Ethio Kids
በልጆች ትምህርትና አጠቃላይ እደገት ላይ እንሰራለን፡፡
Friday, 15 October 2021
"ምግብ የሚያስቸግሩ ልጆችን እንዴት እንመግባቸው" - ዶ/ር ንጉሤ ጫኔ ፤ የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም
Thursday, 16 September 2021
የልጆች ትምህርት ላይ የወላጅ ሚና
ማንኛዉም ወላጅ ልጁ በትምህርቱ ዉጤታማ እንዲሆንለት መርዳት ይችላል፡፡ ወላጆች በየትኛዉም የእድሜና የእዉቀት ደረጃ ላይ ቢሆኑም ፤ በየትኛዉም የስራ ዘርፍ ቢሰማሩም፤ በየትኛዉም የኑሮ ደረጃ ላይ ቢገኙም በልጆች ትምህርት ላይ ከወላጅ የሚጠበቀውን ሚናን ከመወጣት አያግዳቸዉም፡፡
ይህ ማለት ልጅዎን ለመርዳት ልጅዎ ስለሚማራቸዉ የትምህርት ይዘቶች ጥልቅ እዉቀት እንዲኖረዎ ይጠበቃል ማለት አይደለም፡፡ ልጅዎን ለመርዳት የሂሳብ ሊቅ አልያም የሳይንስ አዋቂ መሆን አይጠበቅበዎትም፡፡ ልጅዎ ስለሚማራቸዉ የትምህርት ይዘቶች ምንም አይነት እውቀት ባይኖረዎት እንኳን በልጅዎ የትምህርት አቀባበል ና የጥናት ሁኔታ ላይ ትርጉም ያለዉ ዕገዛ ማድረግ እንደሚችሉ መረዳት ይኖርበዎታል፡፡ እርስዎ ከልጅዎ ፤ ከመምህራንና ከትምህርት ቤቶች ጋር የሚፈጥሩት ጠንካራ ግንኙነት ለልጅዎ የትምህርት ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለዉ፡፡
Wednesday, 15 September 2021
ልጆችና የፊት ጭንብሎች
የኮሮና ወረርሽኝ በአለም ላይ መከሰቱን ተከትሎ ሰዎች ከቤት ውጭ እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ወቅት የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ መጠቀም የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ አስተዋጽኦ እንዳለው በጤና ባለሙያዎች ይነገራል።
ቀደም ባሉት ጊዜያት የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እንዲጠቀሙ የሚመከረው የጤና ባለሙያዎች ብቻ ነበር። አሁን ላይ ግን ማንኛውም ሰው ጭምብሎችን እንዲጠቀም እየተደረገ ይገኛል። ይህ ለብዙ ህፃናት አይተውት የማያውቁት እንግዳ ነገር ይሆንባቸዋል። በተለይ ማስክ እንዲጠቀሙ ሲደረጉ የፍርሀት ብሎም የመደናገጥ ስሜት ሊፈጥርባቸው እንደሚችል ይጠበቃል።
ይህንን ችግር ለማስወገድ ወላጆች ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል?
ሰዎች ማስክ ለምን እንደሚጠቀሙ በቀላል ና በሚገባቸው ቋንቋ ማስረዳት።
ልጆች ማስኩን እንዲያዮትና እንዲነኩት በማድረግ እንዲረዱትና እንዲያውቁት እድል መስጠት።
እርዳታ ማድረግ
አንዳንድ ተዳጊዎችና ትንንሽ ልጆች የፊት ጭንብሎችን ለማድረግ ፍርሀት ሊያድርባቸው ይችላል፡፡ይህንን ለመቀነስ ከወላጆቻቸው ተጨማሪ ክትትልና ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡ወላጆች ጭንብል የማድረግን አስፈላጊነት ለልጆቻቸው ማስረዳት፡አለባቸው፡፡
ልጆች የፊት ጭንብልን ስለመልበስ ምን ይሰማቸዋል?
ይሄ እንደ ልጆቹ እድሜ ደረጃ የሚወሠን ነው፡፡በእድሜ ትንሽ ተለቅ ያሉ ልጆች የፊት ጭንብሎችን ሲያደርጉ ምንም የሚረብሽ ስሜት ላይሰማቸው ይችላል፡፡
ሌሎቹ ደግሞ ጭንብሎቹን ለማድረግ ይጓጓሉ፡፡እንደውም አንዳንዶቹ ልጆች ጭንብሉን ሲያደርጉ የህክምና ባለሞያ የሆኑ ስለሚመስላቸው ደስተኛ ይሆናሉ፡፡
ነገር ግን ለጨቅላ ህፃናት እና ለአንዳንድ ትንንሽ ልጆች ቀላል ላይሆን ይችላል፡፡እነሱን ለማለማመድ የተወሰነ ጊዜ ሊወስድ ይችላል፡፡ይህንንም በቀላሉ እንዲያደርጉ የወላጆች እገዛ ያስፈልጋቸዋል፡፡
የተቀሩት ደግሞ ብስጭት ወይም ፍርሀት ሊሰማቸው ይችላል፡፡ሊያለቅሱ፣ፊታቸውን ሊደብቁ ይችላሉ፡፡ነገር ግን ቤተሠብ እነሱን ለማረጋጋት የራሱን ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
ልጆች የፊት ጭንብል ለማድረግ ለምን ይፈራሉ?
የፊት ጭንብል የፊት ገፃችንን በከፊል ይሸፍናል፡፡ይህ ደግሞ ለትንንሽ ልጆች መሸበርን ይፈጥራል ምክንያቱም ልጆች ደህንነት የሚሰማቸው የሠዎች ፊት ላይ ያለውን እንቅስቃሴ በማየት ነው፡፡
ይህንንም ለመቅረፍ ቤተሰብ በተረጋጋ መንፈስ ስለ ነገሩ ማስረዳት ይጠበቅበታል፡፡ምንም እንኳን ትንንሽ ልጆች ቢሆኑም ልናስተምራቸው የሚገባው አንዳንድ ከሩቅ የሚያስፈሩ የሚመስሉ ነገሮች ቀርበን ስናያቸው እንደማያስፈሩ በመንገር ነው፡፡
ወላጆች ልጆችን የፊት ጭንብል እንዲያረጉ እንዴት ማድረግ ይችላሉ?
ከ 2 አመት በታች ያሉ ልጆችና አዋቃዎች የፊት ጭንብል መጠቀማቸው የበሽታው ስርጭት እንዲቀንስ ይረዳል፡፡ይህንንም ልጆች እንዲያውቁት ማረግ ይገባል፡፡እዚህ ጋር ህጻናት የፊት ጭንብሎችን ያለ ጭንቀት እንዲያረጉ የሚረዱ ነጥቦችን እናንሳ
ልጆች ጭንብላቸውን በፈለጉት መንገድ እንዲያስጌጡ እድል ይስጧቸው፡፡ይህም የባለቤትነት ስሜት እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡ልጆች ጭንብሉ ላይ እንዲስሉበትና የተለያዩ ጌጣ ጌጦችን እንዲለጥፉበት ማድረግ ፍርሀታቸውን ይቀንሳል፡፡
ጭንብሎችን አድርገው ልክ እንደ ሀኪም ከአሻንጉሊቶቻቸው ጋር እንዲጫወቱ ማድረግ የበለጠ ከጭንብሉ ጋር እንዲላመዱ ያደርጋል፡፡
ልጆችዎ ትምህርት ቤት መሄድ ቢጠሉ ምን ያደርጋሉ?
በዩናይትድ ስቴትስ ቴክሳስ ግዛት የጋብቻና የቤተሰብ አማካሪ እንዲሁም በዚሁ ዙሪያ ፀሀፊና አሰልጣኝ የሆኑት ዶክተር ሙላቱ በላይነህ እንደሚያስረዱት ይህ አይነቱ በህፃንነት እድሜ ላይ ትምህርት ቤት የመሄድ ፍራቻ ወይም ጥላቻ የሚከሰተው በእንግሊዘኛው ሰፓሬሽን አንዛይቲ ተብሎ በሚጠራው መለየት የሚፈጥረው ጭንቀት ምክንያት ነው።
ትምህርት ቤት የመሄድ ጥላቻ ወይም ፍራቻ በህፃናት ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የእድሜ ክልል ላይ ባሉ ልጆች ላይ ሊደርስ ይችላል። ለዚህ ምክንያቱ እንደየእድሜያቸው እና የአኗኗራቸው ሁኔታ እንደሚለያይ ዶክተር ሙላቱ ያስረዳሉ።
ሌላው ለልጆች ትምህርት ቤት መጥላት ምክንያት የሚሆነው ደግሞ በቤተሰብ መሃል የሚደርስ ግጭት ወይምበትምህርት ቤት ውስጥ የሚያጋጥም የዝቅተኛነት ስሜት በስነልቦናቸው ላይ የሚያሳድሮ ተፅእኖ እንደሆነ ዶክተር ሙላቱጨምረው ያብራራሉ።
ከዚህም በተጨማሪ በትምህርት ድረጃ ዝቅተኛ መሆንና ከሌሎች ተማሪዎች ጋር አብሮ መሄድ አለመቻልም እንዲሁ ለትምህርት ቤት ጥላቻ አስተዋጽኦ ያደርጋል። በተለይ ወላጆቻቸው ለስራ ወይም ለኑሮ የሚኖሩበትን ቦታ ወይም ሀገር ቀይረው ወደ አዲስ ቦታ ሲሄዱ ይህ አይነቱ ችግር ጎልቶ ሊታይ ይችላል።
ልጆቻቸው ትምህርት ቤት መሄድ የሚያቸግሯቸው ብዙ ወላጆች በቁጣና በቅጣት ልጆችን ወደ ትምርህት ቤት እንዲሄዱለማድረግ ይሞክራሉ። ይህ አይነቱ አካሄድ ግን በተቃራኒው ልጆች እንዲርቁና ሌላ መደበቂያ እንዲፈልጉእንደሚያደርጋቸው የሚያስረዱት ዶክተር ሙላቱ መፍትሄው ለልጆች ግዜ መስጠትና መነጋገር መሆኑን ያሰምሩበታል።
ዶክተር ሙላቱ አክለው ልጆች አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት በትምህርት ቤት እንደመሆኑ መጠን ከትምህርትቤታቸውና ከመምህራኖቻቸው ጋር የቅርብ ግንኙነት መፍጠርም ልጆችን ለመረዳትና ለማገዝ ቁልፍ መሰረት ነው ይላሉ።
ፍቅረሰላምም ልጆቿ ትምህርት ቤታቸውን እንዲለምዱ እና እንዲወዱ ማድረግ የቻለችው፣ በየቀኑየሚያስጨንቃቸውንና የሚረብሻቸውን እንዲያካፍሉ በግልፅ በማናገርና ከትምህርት ቤታቸውና ከመምህራኖቻቸው ጋርበመነጋገር ነበር። ይህን በማድረጓ ልጆቿ ዛሬ ትምህርት ቤታቸውን ከመውደዳቸው በላይ ከጓደኞቻቸው ተግባቢናውጤታማ መሆን ችለዋል።
Saturday, 12 May 2018
የልጅዎን የምግብ ፍላጎት ለመጨመር የሚረዱ 12 ጠቃሚ ምክሮች
የልጆች የምግብ ፍላጎት ማጣት ለበርካታ ወላጆች አስቸጋሪና አሳሳቢ ችግር እየሆነ መጥቷል። አንዳንዴም ቤተሰቡ ውስጥ ውጥረትን ሲፈጥር ይስተዋላል። ወላጆችም ልጆችን እያታለሉ ከመመገብ እስከ ቁጣና ማስፈራራት ድረስ የሚደርሱ መንገዶችን በመከተል ልጀቻቸውን ለመመገብ ሲጥሩ ይታያል። ይህንን ችግር ለመቅረፍ የሚረዱና የምግብ ፍላጎትን ለመጨመር የሚረዱ ሳይንሳዊ መንገዶች እነሆ ብለናል ። ያንብቡና ለሌሎችም ያጋሩ።
1. ልጅዎ ሁል ጊዜ ቁርስ መመገቡን ያረጋግጡ
ጥሩ እና ጤናማ ቁርስ መመገብ የልጅዎን የመመገብ ፍላጎት ይጨምራል።
2. ልጆች ምግብ ከመውሰዳቸው ከ30 ደቂቃዎች በፊት ውሃ ይስጧቸው
ልጆች ማለዳ ከመኝታቸው እደተነሱ ወተት ከመጠጣታቸው በፊት ውሃ እንዲጠጡ ይመከራል ። በተጨማሪም ምግብ ከመጀመራቸው ከግማሽ ሰዓት በፊት ውሃ ቢሰጣቸው የምግብ ፍላጎታቸ እንዲጨምር ያደርጋል።
3. ወተት ብዛት አይመገቡ
ጥቂት የምግብ ፍላጎት ያላቸው ብዙ ሕፃናት 'በጣም ብዙ ወተት' የመጠጣት ልምድ አላቸው ። ይህም የምግብ ፍላጎታቸውን የባሰ ሊቀንሰው ይችላል ። በመሆኑም የወተት መጠን በመቀነስ በሌሎች ተመሳሳይ ፈሳሽ ምግቦች ይተኩላቸው ።
4. የሚወዱትን ምግብ ይስጧቸው
የምግብ ፍላጎት ችግር ያለባቸው ልጆች አንዳንድ ጊዜ የሰለቻቸውን የምግብ አይነት መመልከት ሁሉ ሲያስጠላቸው ይታያል ።
ይህ የልጅዎ ሁኔታ ከሆነ የምግብ።ፍላጎታቸውን ለማነሳሳት በመጀመሪያ የሚወዱትን የምግብ አይነት መጀመሪያ ላይ ለማቅረብ ይሞክሩ።
5. በትንሽ በትንሹ ይስጧቸው
ለመጀመሪያ ጊዜ በጣም ትንሽ የምግብ መጠን ይስጧቸው ። ይህ ትንሽ የምግብ ይዘት በተራው የምግብ ፍላጎት ያሻሽላል ።
ለልጆች ጥቂት ምግብ ብቻ ይስጡ ይህም ቀስ በቀስ የምግብ ፍላጎታቸው ይጨምራል.
እራሳቸውን በራሳቸው መብላት እስኪጀምሩ እና በእራሳቸውን መጠን እስኪወስዱ ድረስ ትንሽ ትንሹን መስጠት አለብዎ።
6. ቅባት የበዛበት ምግቦ አይስጧቸው
ምክንያቱም የበዛ የቅባት ይዘት የልጅዎን የምግብ ፍላጎት የባሰ እንዲቀንስ ያደርጋል ።
7. ልጅዎን እንዲጫወትና እንዲንቀሳቀስ ያድርጉ
ስፖርት መስራትና ብዙ ሀይል እንደሚወስድ የታወቀ ነው ይህም የምግብ ፍጆችን እንዲጨምር ያደርጋል።
ልጅዎ ዝቅተኛ የምግብ ፍላጎት ካለው የጨዋታ ጊዜውን ይጨምሩ ረሃብ ተመልሶ ሲመጣ ያዩታል!
8. በጣም ሞቃት ከሆኑ አየር እንዲገባ ያድርጉ
አዎ እውነት ነው! በቤት ውስጥ በጣም ሞቃት ከሆነ የምግብ ፍላጎት ይቀንሳል። ልጅዎን በሚመግቡበት ወቅት ክፍት መስኮት አጠገብ በመሆን ንጹህ አየር እንዲገባ ያድርጉ ለውጡን ያስተውሉታል።
9. ትኩስ የሎሚ ጭማቂ ይስጡ
የሎሚ ጭማቂ የመመገብን እና የምግብ ፍላጎትን ያሻሽላል።
10. በምግብ ሰዓት ጭንቀቶች ያስወግዱ
በምግብ ጊዜያትአላስፈላጊ ጭንቀቶችን ያስወግዱ ። ልጄ ምግብ አልበላ አለ በማለት የሚያሳዮት ጭንቀት የልጆችን ስሜት ሊረብሽና የባሰ ፍላጎታቸውን ሊቀንስ ይችላል ።
11. የዚንክ ንጥረ ነገርን ይጨምሩ
ዚንክ የምግብ ፍላጎት ለመገንባት ይረዳል። የስንዴና የለውዝ ዘሮች በሰውነት ውስጥ የዚንክ ደረጃ ለማሻሻል ጥሩ ናቸው። በልጅዎ ምግቦች ውስጥ እነዚህን ነገሮች ማካተት ይሞክሩ።
12. አትክልትና ፍራፍሬን አዘውትረው ይመግቡ
አትክልትና ፍራፍሬ ምግቦች የምግብ ፍላጎት ለመገንባት ይረዳሉ። ምግብን በማዋሃድ ሜታቦሊዝም እንዲጨምር ይሠራሉ ።
በመጨረሻም ልጅዎ እጅግ የከፋ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ችግር ካለበት ሀኪምዎን ማማከር አይርሱ ።
Wednesday, 9 May 2018
10 Tips on Reading with Your Child
As a parent or caregiver, you can play an important role in helping your child to learn to read.
Here are some tips on how you can help to make learning to read a positive experience for your child.
1. Choose a quiet time
Set aside a quiet time with no distractions. Ten to fifteen minutes is usually long enough.
2. Make reading fun
Make reading fun. Sit with your child. Try not to pressure your child. If your child loses interest then do something else and try again another time.
3. Maintain the flow
If your child mispronounces a word do not interrupt immediately. Instead allow them time to self‐correct. But it is better to tell a child some unknown words to maintain the flow rather than insisting on trying to build them all up from the sounds of the letters. If your child does try to 'sound out' words, encourage the use of letter sounds rather than 'alphabet names'.
4. Stay positive
If your child says something nearly right to start with that is fine. Don't say 'No. That's wrong,' but 'Let's read it together' and point to the words as you say them. Boost your child's confidence with constant praise for even the smallest achievement.
5. Success is the key
It is always a mistake to give a child a book that is too difficult. Remember 'Nothing succeeds like success'. Until your child has built up his or her confidence, it is better to choose easier books. Struggling with a book with many unknown words is frustrating for a child and can lead to him or her becoming a reluctant reader.
6. Regular practice
Try to read with your child every day. 'Little and often' is best.
7. Communicate
Your child will also be learning to read in school. Ask them about what books they are reading in school. Your child will then know that you are interested in their progress and that you value reading.
8. Talk about the books
There is more to being a good reader than being able to read the words accurately. It’s just as important is being able to understand what has been read. Always talk to your child about the book; about the pictures, the characters, how they think the story will end, their favourite part. You will then be able to see how well they have understood and you will help them to develop good comprehension skills.
9. E-books are just as good as paper books for learning to read
If you are reading this now, then you have access to hundreds of books that you can enjoy reading with your children – and we are adding more all the time.
10. Variety is important
All reading is good! Not just books, but also magazines, newspapers, road signs – even text messages.
***
THE END
Thursday, 12 April 2018
የልጆች ትምህርት ላይ የወላጅ ሚና
ማንኛዉም ወላጅ ልጁ በትምህርቱ ዉጤታማ እንዲሆንለት መርዳት ይችላል፡፡ ወላጆች በየትኛዉም የእድሜና የእዉቀት ደረጃ ላይ ቢሆኑም ፤ በየትኛዉም የስራ ዘርፍ ቢሰማሩም፤ በየትኛዉም የኑሮ ደረጃ ላይ ቢገኙም በልጆች ትምህርት ላይ ከወላጅ የሚጠበቀውን ሚናን ከመወጣት አያግዳቸዉም፡፡
ይህ ማለት ልጅዎን ለመርዳት ልጅዎ ስለሚማራቸዉ የትምህርት ይዘቶች ጥልቅ እዉቀት እንዲኖረዎ ይጠበቃል ማለት አይደለም፡፡ ልጅዎን ለመርዳት የሂሳብ ሊቅ አልያም የሳይንስ አዋቂ መሆን አይጠበቅበዎትም፡፡ ልጅዎ ስለሚማራቸዉ የትምህርት ይዘቶች ምንም አይነት እውቀት ባይኖረዎት እንኳን በልጅዎ የትምህርት አቀባበል ና የጥናት ሁኔታ ላይ ትርጉም ያለዉ ዕገዛ ማድረግ እንደሚችሉ መረዳት ይኖርበዎታል፡፡ እርስዎ ከልጅዎ ፤ ከመምህራንና ከትምህርት ቤቶች ጋር የሚፈጥሩት ጠንካራ ግንኙነት ለልጅዎ የትምህርት ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለዉ፡፡
"ምግብ የሚያስቸግሩ ልጆችን እንዴት እንመግባቸው" - ዶ/ር ንጉሤ ጫኔ ፤ የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም
ከአንድ እስከ ሦሥት ዓመት ያሉ ልጆች መደበኛ አመጋገብ የላቸውም። አንድ ቀን በድንብ ይበላሉ ሌላ ቀን ደግሞ ፈጽመው ምግብ መንካት አይፈልጉም። ቁርስ በደንብ በልተው ምሳ ላይፈልጉ ይችላሉ። ይህ የተለመደ ፀባያቸው ስለሆነ ...

-
የልጆች የምግብ ፍላጎት ማጣት ለበርካታ ወላጆች አስቸጋሪና አሳሳቢ ችግር እየሆነ መጥቷል። አንዳንዴም ቤተሰቡ ውስጥ ውጥረትን ሲፈጥር ይስተዋላል። ወላጆችም ልጆችን እያታለሉ ከመመገብ እስከ ቁጣና ማስፈራራት ድረስ የ...
-
ከአንድ እስከ ሦሥት ዓመት ያሉ ልጆች መደበኛ አመጋገብ የላቸውም። አንድ ቀን በድንብ ይበላሉ ሌላ ቀን ደግሞ ፈጽመው ምግብ መንካት አይፈልጉም። ቁርስ በደንብ በልተው ምሳ ላይፈልጉ ይችላሉ። ይህ የተለመደ ፀባያቸው ስለሆነ ...
-
የልጆች ትምህርት ላይ የወላጅ ሚና ማንኛዉም ወላጅ ልጁ በትምህርቱ ዉጤታማ እንዲሆንለት መርዳት ይችላል፡፡ ወላጆች በየትኛዉም የእድሜና የእዉቀት ደረጃ ላይ ቢሆኑም ፤ በየትኛዉም የስራ ዘርፍ ቢሰማሩም፤ በየ...