የልጆች ትምህርት ላይ የወላጅ ሚና
ማንኛዉም ወላጅ ልጁ በትምህርቱ ዉጤታማ እንዲሆንለት መርዳት ይችላል፡፡ ወላጆች በየትኛዉም የእድሜና የእዉቀት ደረጃ ላይ ቢሆኑም ፤ በየትኛዉም የስራ ዘርፍ ቢሰማሩም፤ በየትኛዉም የኑሮ ደረጃ ላይ ቢገኙም በልጆች ትምህርት ላይ ከወላጅ የሚጠበቀውን ሚናን ከመወጣት አያግዳቸዉም፡፡
ይህ ማለት ልጅዎን ለመርዳት ልጅዎ ስለሚማራቸዉ የትምህርት ይዘቶች ጥልቅ እዉቀት እንዲኖረዎ ይጠበቃል ማለት አይደለም፡፡ ልጅዎን ለመርዳት የሂሳብ ሊቅ አልያም የሳይንስ አዋቂ መሆን አይጠበቅበዎትም፡፡ ልጅዎ ስለሚማራቸዉ የትምህርት ይዘቶች ምንም አይነት እውቀት ባይኖረዎት እንኳን በልጅዎ የትምህርት አቀባበል ና የጥናት ሁኔታ ላይ ትርጉም ያለዉ ዕገዛ ማድረግ እንደሚችሉ መረዳት ይኖርበዎታል፡፡ እርስዎ ከልጅዎ ፤ ከመምህራንና ከትምህርት ቤቶች ጋር የሚፈጥሩት ጠንካራ ግንኙነት ለልጅዎ የትምህርት ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለዉ፡፡
No comments:
Post a Comment