የኮሮና ወረርሽኝ በአለም ላይ መከሰቱን ተከትሎ ሰዎች ከቤት ውጭ እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ወቅት የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ መጠቀም የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ አስተዋጽኦ እንዳለው በጤና ባለሙያዎች ይነገራል።
ቀደም ባሉት ጊዜያት የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እንዲጠቀሙ የሚመከረው የጤና ባለሙያዎች ብቻ ነበር። አሁን ላይ ግን ማንኛውም ሰው ጭምብሎችን እንዲጠቀም እየተደረገ ይገኛል። ይህ ለብዙ ህፃናት አይተውት የማያውቁት እንግዳ ነገር ይሆንባቸዋል። በተለይ ማስክ እንዲጠቀሙ ሲደረጉ የፍርሀት ብሎም የመደናገጥ ስሜት ሊፈጥርባቸው እንደሚችል ይጠበቃል።
ይህንን ችግር ለማስወገድ ወላጆች ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል?
ሰዎች ማስክ ለምን እንደሚጠቀሙ በቀላል ና በሚገባቸው ቋንቋ ማስረዳት።
ልጆች ማስኩን እንዲያዮትና እንዲነኩት በማድረግ እንዲረዱትና እንዲያውቁት እድል መስጠት።
እርዳታ ማድረግ
አንዳንድ ተዳጊዎችና ትንንሽ ልጆች የፊት ጭንብሎችን ለማድረግ ፍርሀት ሊያድርባቸው ይችላል፡፡ይህንን ለመቀነስ ከወላጆቻቸው ተጨማሪ ክትትልና ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡ወላጆች ጭንብል የማድረግን አስፈላጊነት ለልጆቻቸው ማስረዳት፡አለባቸው፡፡
ልጆች የፊት ጭንብልን ስለመልበስ ምን ይሰማቸዋል?
ይሄ እንደ ልጆቹ እድሜ ደረጃ የሚወሠን ነው፡፡በእድሜ ትንሽ ተለቅ ያሉ ልጆች የፊት ጭንብሎችን ሲያደርጉ ምንም የሚረብሽ ስሜት ላይሰማቸው ይችላል፡፡
ሌሎቹ ደግሞ ጭንብሎቹን ለማድረግ ይጓጓሉ፡፡እንደውም አንዳንዶቹ ልጆች ጭንብሉን ሲያደርጉ የህክምና ባለሞያ የሆኑ ስለሚመስላቸው ደስተኛ ይሆናሉ፡፡
ነገር ግን ለጨቅላ ህፃናት እና ለአንዳንድ ትንንሽ ልጆች ቀላል ላይሆን ይችላል፡፡እነሱን ለማለማመድ የተወሰነ ጊዜ ሊወስድ ይችላል፡፡ይህንንም በቀላሉ እንዲያደርጉ የወላጆች እገዛ ያስፈልጋቸዋል፡፡
የተቀሩት ደግሞ ብስጭት ወይም ፍርሀት ሊሰማቸው ይችላል፡፡ሊያለቅሱ፣ፊታቸውን ሊደብቁ ይችላሉ፡፡ነገር ግን ቤተሠብ እነሱን ለማረጋጋት የራሱን ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
ልጆች የፊት ጭንብል ለማድረግ ለምን ይፈራሉ?
የፊት ጭንብል የፊት ገፃችንን በከፊል ይሸፍናል፡፡ይህ ደግሞ ለትንንሽ ልጆች መሸበርን ይፈጥራል ምክንያቱም ልጆች ደህንነት የሚሰማቸው የሠዎች ፊት ላይ ያለውን እንቅስቃሴ በማየት ነው፡፡
ይህንንም ለመቅረፍ ቤተሰብ በተረጋጋ መንፈስ ስለ ነገሩ ማስረዳት ይጠበቅበታል፡፡ምንም እንኳን ትንንሽ ልጆች ቢሆኑም ልናስተምራቸው የሚገባው አንዳንድ ከሩቅ የሚያስፈሩ የሚመስሉ ነገሮች ቀርበን ስናያቸው እንደማያስፈሩ በመንገር ነው፡፡
ወላጆች ልጆችን የፊት ጭንብል እንዲያረጉ እንዴት ማድረግ ይችላሉ?
ከ 2 አመት በታች ያሉ ልጆችና አዋቃዎች የፊት ጭንብል መጠቀማቸው የበሽታው ስርጭት እንዲቀንስ ይረዳል፡፡ይህንንም ልጆች እንዲያውቁት ማረግ ይገባል፡፡እዚህ ጋር ህጻናት የፊት ጭንብሎችን ያለ ጭንቀት እንዲያረጉ የሚረዱ ነጥቦችን እናንሳ
ልጆች ጭንብላቸውን በፈለጉት መንገድ እንዲያስጌጡ እድል ይስጧቸው፡፡ይህም የባለቤትነት ስሜት እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡ልጆች ጭንብሉ ላይ እንዲስሉበትና የተለያዩ ጌጣ ጌጦችን እንዲለጥፉበት ማድረግ ፍርሀታቸውን ይቀንሳል፡፡
ጭንብሎችን አድርገው ልክ እንደ ሀኪም ከአሻንጉሊቶቻቸው ጋር እንዲጫወቱ ማድረግ የበለጠ ከጭንብሉ ጋር እንዲላመዱ ያደርጋል፡፡