Thursday, 12 April 2018







የልጆች ትምህርት ላይ የወላጅ ሚና
 
ማንኛዉም ወላጅ ልጁ በትምህርቱ ዉጤታማ እንዲሆንለት መርዳት ይችላል፡፡ ወላጆች በየትኛዉም የእድሜና የእዉቀት ደረጃ ላይ ቢሆኑም ፤ በየትኛዉም የስራ ዘርፍ ቢሰማሩም፤ በየትኛዉም የኑሮ ደረጃ ላይ ቢገኙም በልጆች ትምህርት ላይ ከወላጅ የሚጠበቀውን ሚናን ከመወጣት አያግዳቸዉም፡፡ 




ይህ ማለት ልጅዎን ለመርዳት ልጅዎ ስለሚማራቸዉ የትምህርት ይዘቶች ጥልቅ እዉቀት እንዲኖረዎ ይጠበቃል ማለት አይደለም፡፡ ልጅዎን ለመርዳት የሂሳብ ሊቅ አልያም የሳይንስ አዋቂ መሆን አይጠበቅበዎትም፡፡ ልጅዎ ስለሚማራቸዉ የትምህርት ይዘቶች ምንም አይነት እውቀት ባይኖረዎት እንኳን በልጅዎ የትምህርት አቀባበል ና የጥናት ሁኔታ ላይ ትርጉም ያለዉ ዕገዛ ማድረግ እንደሚችሉ መረዳት ይኖርበዎታል፡፡ እርስዎ ከልጅዎ ፤ ከመምህራንና ከትምህርት ቤቶች ጋር የሚፈጥሩት ጠንካራ ግንኙነት ለልጅዎ የትምህርት ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለዉ፡፡







አድናቆት

ስለእራሱ ጥሩ ነገር እየተነገረው ያደገ ልጅ ማድነቅን ይማራል
አግባብነት ያለው ማበረታቻ እያገኘ ያደግ ልጅ በእራስ መተማመንን ይማራል
መቻቻል በሰፈነበት ሁኔታ ያደገ ልጅ ትዕግስተኝነትን ይማራል
ልጅ ከአድሎ ነጻ በሆነ ሁኔታ በአግባቡ ካደገ ፍትህን ይማራል
ልጅ ዋስትናና ደህንነት በተመላበት ኑሮ ካደገ ሰውን ማመንን ይማራል
ልጅን በማንነቱ ተቀብለን በማቅረብ ካሳደግነው ምሉዕ ፍቅር ከአለም ይማራል
ጥላቻ በተመላበት አካባቢ ያደገ ልጅ ጠባጫሪነትን ይማራል
ልጅ በሃፍረት ካደገ የጥፋተኝነት መንፈስን ይማራል
…. እንዳለው ዶርቲ ሎው
በየትኛውም ስፍራ የሚኖር የሰው ልጅ ህጻንም ይሁን አዋቂ አድናቆትንና ሙገሳን ይወዳል እንዲሁም ይፈልጋል፡፡ መደነቅ በሰዎች ዘንድ ትኩረት ማግኘታቸንን ስለሚያመላክት ተደናቂው ክብርና የመንፈስ ከፍታ ይሰማዋል፡፡ “አንበሳ ፤ ወንድ ነህ! በጣም ድንቅ ስራ ነው የሰራኸው…..ወዘተ” ሰዎች አድናቆትን ለመግለጽ የሚጠቀሙባቸው ቃላት ናቸው፡፡ አድናቆትን በተመለኩ ብዙ ምሁራን በጉዳዩ ላይ ተከራክረዋል የተለያዩ ጥናቶችንም አካሄደዋል፡፡ ምሁራኑ እንደ ርዕሰ ጉዳዮቻቸው ያገኙት ውጤትም ያንኑ ያህል ይለያያል፡፡ አንዳንዶች በጥናታቸው መሠረት አድናቆት ተስፍ ለቆረጡና ምንም ማድረግ አንችልም ብለው ለተቀመጡት እንደ ጉዞ ስንቅ በማገልገል እንደገና ተስፋቸውን አለምልመው ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ ይራዳቸዋል ሲሉ በተቃራኒው አድናቆት በተለይ የልጆችን መነሳሳት ይቀንሳል ፤ ጫናዎችን እንዳይቋቋሙ ያደርጋል ከፍ ሲልም ጥገኝነትን ይፈጥራል ይላሉ፡፡
የሂሁማኒሰቲክ ሳይኮሎጂ አቀንቃኞችም የልጆችን ባህሪ እየመረጥን ማድነቃችን ማንነታቸውን ሙሉ በሙሉ እንዳይቀበሉና እያደጉ ሲሄዱም ፤ መሆን በሚፈልጉትና (ideal self-concept) በሆኑት ማንነታቸው (real self-concept) መካከል ከፍተኛ ልዩነት ሊፈጠር ይችላል፡፡ ይህም ለስነ-ልቡና መታወክ አስተዋጽኦ ሊፈጥር ይችላል ይሉናል፡፡ ሂውማኒስቲኮቹ የሚያበረታቱት አንድን ሰው በሙሉ ከእነ እንከኑ መቀበልን ነው (unconditional positive regard)፡፡ ለነገሩማ ከወደዱ ከነ ንፍጡ ነው ይባል አይደል እንዴ በሀገራችን አባባል፡፡
አልፊ ኮን (2005)
በአንቶኒዮ ሙላ

"ምግብ የሚያስቸግሩ ልጆችን እንዴት እንመግባቸው" - ዶ/ር ንጉሤ ጫኔ ፤ የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም

ከአንድ እስከ ሦሥት ዓመት ያሉ ልጆች መደበኛ አመጋገብ የላቸውም። አንድ ቀን በድንብ ይበላሉ ሌላ ቀን ደግሞ ፈጽመው ምግብ መንካት አይፈልጉም። ቁርስ በደንብ በልተው ምሳ ላይፈልጉ ይችላሉ። ይህ የተለመደ ፀባያቸው ስለሆነ ...